የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ| የግዮን ንግስቶች የነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል ማደስ ጀምረዋል

የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ| የግዮን ንግስቶች የነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል ማደስ ጀምረዋል

ባህር ዳር ከተማ የስድስት ተጫዋቾቹን ውል አራዘመ

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የሚሳተፈው ባህር ዳር ከተማ ለቀጣዮቹ የውድድር ዘመናት ስብስቡን ለማጠናከር እና የነበሩትን ቁልፍ ተጫዋቾች ለማቆየት ባደረገው እንቅስቃሴ የስድስት ተጫዋቾቹን ውል ማራዘሙን ይፋ አድርጓል። በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ቀርበው ውላቸውን ያደሱት እነዚህ ተጫዋቾች በክለቡ የመቆያ ጊዜያቸውን በይፋ አራዝመዋል።

በዚህም መሰረት ደመቀች ዳልጋ፣ ወርቅነሽ መሰለ እና ማናየሽ ተስፋዬ እያንዳንዳቸው ለሁለት ሁለት ዓመታት የሚቆይ ተጨማሪ ውል ሲፈርሙ ቃልኪዳን ተስፋዬ፣ ማህደር ባይህ እና አሶሬ ሃይሶ ደግሞ ለተጨማሪ አንድ ዓመት በክለቡ ለመቆየት የሚያስችላቸውን ውል ማደሳቸውን አረጋግጠዋል።