ከጦና ንቦቹ ጋር ቆይታ የነበረው ወጣቱ አማካይ ኢዮብ ተስፋዬ ለንግድ ባንክ ለመጫወት ተስማምቷል።
የ2016 የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነባር ተጫዋቾችን ውል በማራዘም እና ሙሉቀን አዲሱን የመጀመርያ ፈራሚ በማድረግ ወደ ዝውውር የገቡ ሲሆን አሁን የተስፈኛውን አማካይ ኢዮብ ተስፋዬን ለማስፈረም መስማማታቸውን አውቀናል።
ዕድገት እና የእግርኳስ መነሻውን በወላይታ ድቻ ያደረገው ኢዮብ ሁለተኛ መለያውን ለንግድ ባንክ ሊያደርግ ለሁለት ዓመት መስመማቱን አውቀናል።

