ከሀዋሳ ከተማ ጋር ቆይታ የነበረው ተከላካይ ወደ ሀዲያ ሆሳዕና አምርቷል።

በአሰልጣኝ ሳምሶን አየለ የሚመሩት ሀድያ ሆሳዕናዎች ወደ ዝውውሩ በመግባት ከዚህ ቀደም ያሬድ ታደሰን እና ቢንያም ጌታቸውን ማስፈረማቸው ይታወቃል። አሁን የመሐል ተከለካይ ወንድማገኝ ማዕረግን ማስፈረማቸው እርግጥ ሆኗል።
በሀዋሳ ከተማ የእግርኳስ መነሻውን ያደረገው ወንድማገኝ በወልቂጤ ከተማ እንዲሁም ያለፉትን ሁለት ዓመት በሀዋሳ ከተማ ሲጫወት ቆይቶ አሁን መዳረሻው ሀድያ ሆሳዕና ሆኗል።

