ሐይቆቹ የመስመር አጥቂ ለማስፈረም ተስማምተዋል

ሐይቆቹ የመስመር አጥቂ ለማስፈረም ተስማምተዋል

ቡድናቸውን በማጠናከር ላይ የሚገኙት ሀዋሳ ከተማዎች የመስመር አጥቂ ወደ ስብሰባቸው ቀላቅለዋል።

የአሰልጣኝ ተመስገን ዳና እና የነባር ተጫዋቾቹን ውል ካራዘሙ በኋላ በለቀቁባቸው ተጫዋቾች ምትክ ወደ ዝውውሩ ገብተው አዳዲስ ተጫዋቾች እያስፈረሙ የሚገኙት ሐይቆቹ አሁን ደግሞ የመስመር አጥቂውን ቃልኪዳን ዘላለምን ማስፈረማቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

ከኢትዮጵያ ቡና ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ ክለቡን በፕሪሚየር ሊጉ በማገልገል የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው ቃልኪዳን በመቀጠል በደደቢት ፣ ሰበታ ከተማ ፣ ወላይታ ድቻ እና ፋሲል ከነማ ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ በቀጣይ ለሀዋሳ ከተማ ለመጫወት ተስማምቷል።