አንዋራ ሙራድ ወደ አሳዳጊው ቤቱ ተመልሷል

አንዋራ ሙራድ ወደ አሳዳጊው ቤቱ ተመልሷል

ያለፉትን ሁለት ዓመታት በዐፄዎቹ ቤት ቆይታ የነበረው አንዋር ሙራድ ወደ እናት ቤቱ ተመልሷል።

የእግርኳስ ህይወቱን በኢትዮ ኤሌክትሪክ ታዳጊ እና ዋናው ቡድን አድርጎ ብዙ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቶ ያለፉትን ሁለት ዓመት በፋሲል ከነማ ቆይታ ያደረገው አጥቂው አንዋር ሙራድ ወደ እናት ቤቱ ኤሌክትሪክ ተመልሶ ለመጫወት ተስማምቷል።

አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ ከትናንት ጀምሮ ወደ ዝውውሩ የገቡ ሲሆን ፍራኦል መንግስቱን ፣ አማኑኤል ግዛቸው እና እሱባለው ሙሉጌታን አስፈርመው የአቤል ሀብታሙን ውል ሲያራዝሙ አሁን ደግሞ አንዋርን ለሁለት ዓመት አስፈርመዋል።