ኢትዮ ኤሌክትሪክ የአራት ወጣቶች ውል አራዘመ

ኢትዮ ኤሌክትሪክ የአራት ወጣቶች ውል አራዘመ

በትናንትናው ዕለት ወደ ዝውውር ገበያ የወጡት ኤሌክትሪኮች የነባር ተጫዋቾችን ውል አራዘሙ።

በትናንትናው ዕለት ወደ ዝውውሩ መስኮቱ ገብተው
ፍራኦል መንግስቱ ፣ አንዋር ሙራድ እንዲሁም በከፍተኛ ሊጉ ደሴ ከተማ ጥሩ ዓመት ያሳለፉት ከፍተኛ ግብ አቆጣሪው አማኑኤል ግዛቸው እና  እሱባለው ሙሉጌታ ለማስፈረም ተስማምተው የአቤል ሀብታሙን ውል ለማራዘም ከስምምነት የደረሱት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች አሁን ደግሞ አራት ተጫዋቾ በቡድኑ ለማቆየት ከስምምነት ደርሰዋል።

ከክለቡ ሁለተኛ ቡድን አድገው ዋናው ቡድኑን በማገልገል የቆዩት ግብ ጠባቂው ኪሩቤል ኃይሉ ፣ አማካዩ ሙከረብ ረሺድ እና የግራ መስመር ተከላካዩ ናትናኤል ዱባለ እንዲሁም ከሱሉልታ ከተማ ክለቡን ተቀላቅሎ ግልጋሎት በመስጠት የቆየው የመስመር አጥቂው አብዱልመጅድ ሁሴን በክለቡ ያላቸውን ውል ለማራዘም የተስማሙ ተጫዋቾች ናቸው።