ከቀናት በፊት ወደ ሀላባ ከተማ ለማምራት ከስምምነት ደርሶ የነበረው ተጫዋች በወልዋሎ ውሉን ለማራዘም ከስምምነት ደርሳል
ከቀናት በፊት ወደ አዲስ አዳጊው ሀላባ ከተማ ለማምራት ከስምምነት ደርሶ የነበረው የግራ መስመር ተከላካዩ ኪሩቤል ወንድሙ አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት ባገለገለበት ወልዋሎ ውሉን ለማራዘም ከስምምነት ደርሷል። ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ለገጣፎ ለገዳዲ ማገልገል የቻለው የግራ መስመር ተከላካዩ በቡድኑ ለመቆየት የተስማማ አምስተኛ ተጫዋች ሆኗል።


