በሲዳማ ቡና የቻምፕዮንነት ጉዞ ጥሩ አገልግሎት የሰጠው አማካዩ አዲስ ክለብ ለማግኝት ተቃርቧል።
በሲዳማ ቡና ታዳጊና ዋናው ቡድን በመጫወት እግርኳስን የጀመረው እና በአዳማ ከተማ ፣ በድሬደዋ ከተማ ቆይታ ካደረገ በኋላ ከሁለት ዓመት በፊት ዳግም ወደ አሳዳጊው ክለብ ሲዳማ ቡና ተመልሶ ይጫወት የነበረው ዮሴፍ ዮሐንስ ከሲዳማ ቡና ጋር ይቀጥላል ተብሎ ሲጠበቅ ወደ ሌላ ክለብ ለማምራት ከጫፍ ደርሷል።
አማካዩ ዘንድሮ አብዛኛው ጨዋታዎች ላይ ተሳትፎ በማድረግ እና ጎል በማስቆጠር ጭምር ሲዳማ ቡና የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ ትልቁን ሚና ከተወጡ ተጫዋቾች መከከል አንዱ ሲሆን ሲዳማ ቡና ጋር አብሮ እንደማይቀጥል እረግጥ መሆኑ ከታወቀበት ጊዜ አንስቶ ስሙ ከተለያዮ ክለቦች ጋር ቢነሳም መዳረሻው ለፋሲል ከነማ ለሁለት ዓመት እንደፈረመ አውቀናል።

