የኪሩቤል ወንድሙ ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኗል

የኪሩቤል ወንድሙ ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኗል

የግራ መስመር ተከላካዮ ኪሩቤል ወንድሙ ከሦስት ክለብ ጋር ለመጫወት መስማማቱ መነጋገሪያነቱ ቀጥሏል።

ከቀናት በፊት ወደ አዲስ አዳጊው ሀላባ ከተማ ለማምራት ከስምምነት ደርሶ የነበረው የግራ መስመር ተከላካዩ ኪሩቤል ወንድሙ አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት ባገለገለበት ወልዋሎ ውሉን ለማራዘም ከስምምነት መድረሱን መግለፃችን ይታወሳል። አሁን በደረሰን መረጃ መሠረት ደግሞ ከቀናት በፊት በዕለተ ቅዳሜ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቅድመ ስምምነት እንደፈረመ አረጋግጠናል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጫዋቹ ከክለቡ ጋር ቅድመ ስምምነት እንደፈረመና ተጫዋቹን የግሉ ማድረጉን በመግለፅ ለፌዴሬሽኑ ደብዳቤ ለማስገባት በዝግጅት እንደሚገኝም አውቀናል።