የዋልያዎቹ የዝግጅት የመጀመሪያ ቀን ውሎ

የዋልያዎቹ የዝግጅት የመጀመሪያ ቀን ውሎ

በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመርያ ቀን ውሎ እንዴት ነበር

በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚሰለጥነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጪው መስከረም ወር ለሚያደርጋቸው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ይረዳው ዘንድ ከቀናት በፊት ለ 39 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ትናንት ጁፒተር ሆቴል መሰባሰብ ችሏል።

– በዛሬው ዕለተም በአልጣኙ ጥሪ ከተደረገላቸው 39 ተጫዋቾች መካከል 31 የቡድኑ አባላት መገኘታቸው አውቀናል።

– ማለዳ ባደረስናቹ ዝርዝር መረጃ መሠረት የሲዳማ ቡናዎቹ አቤል ያለው፣ ያሬድ ባዬ ፣ ብርሃኑ በቀለ፣ መስፍን ታፈሰ፣ ደግፌ አለሙ እና ቢንያም በላይ ያልተገኙ ሲሆን ምን አልባትም በጨዋታው መቃረቢያ ወቅት ቡድኑን ሊቀላቀሉ ይችላሉ።

– እንዲሁም በኩዌት ሊግ አል አረቢ ክለብ የሚገኘው ከንዓን ማርክነህ እና ሌላኛው በኩዌት አል ፋሂሊ ያለው ጋቶች ፓኖም ቡድኑን ያልተቀላቀሉ ሲሆን በፊፋ ካላንደር መሰረት ወደ ጨዋታው መዳረሻ ላይ የስብስቡ አካል ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

– ቡድኑ የመጀመርያ የዝግጅት ቀኑን ዛሬ ከሰዓት ዘጠኝ ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ለማድረግ ቀጠሮ ይዞ የነበረ ቢሆንም በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የልምምድ መርሐ ግብሩ ሳያከናውን ቀርቷል።

– ሆኖም እዛው ባረፉበት ጂፒተር ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ ከአንድ ሰዓት በላይ የቆየ የንድፈ ሀሳብ ስልጠናዎችን ወስደዋል።

– የአየር ሁኔታው በዚህ ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ በብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ማድረጉ የሚቀጥል ከሆነ ምን አልባት የዝግጅት ከተማው ሊቀየር እንደሚችል ይገመታል።

– የህክምናው ባለሙያው ብሩክ ደበበ ከሲዳማ ቡና ጋር ሌላ ሀላፊነት ያለበት በመሆኑ በምትኩ ዳግማዊ ሚኒሊክ መተካቱን አስቀድመን ገልፀን ነበር።

– ቡድኑ የመጀመርያዎቹ የዝግጅት ሳምንታት የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች እንደሚያከናውን ይጠበቃል።

– ፌዴሬሽኑ ለብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅት ይረዳው ዘንድ የአቋም መለኪያ ጨዋታዎችን ለማዘጋጀት እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም አውቀናል።

ሶከር ኢትዮጵያም እያንዳንዱ ኩነቶች እየተከታተለች ወደ እናተ የምታደርስ ይሆናል።