ሲዳማ ቡና ሦስት የወጣት ቡድን ተጫዋቾች ወደ ዋናው ቡድን አሳደገ።

ለካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ዝግጀት በሀዋሳ እያደረጉ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች ከ20 በታች ቡድን ላይ ጥሩ እንቅስቃሴ ያደረጉት ሦስት ታዳጊዎችን ወጀ ዋናው ቡድን ማሳደጋቸውን አውቀናል።
የወጣቶች ቡድን ለሁለት ተከታታይ ዓመት የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ሲያሳኩ የቡድን አባል የነበረው እና የ2017 ዓም ኮከብ ግብ ጠባቂ ሆኖ ያጠናቀቀው ግብ ጠባቂው ትንሳኤ ማርቆስ፣ ተመላላሽ ተከላካይ ሆኖ የተከላካይ መስመሩን ሲመራ የነበረው ሁሴን ጣሃ እና ዘንድሮ ውድድሩን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ የጨረሰው መሳይ ዩሐንስ ወደ ዋናው ቡድን አድገው ዛሬ ረፋድ ላይ ቡድኑ ልምምድ ሲሰራ ሶስቱም መስራት ችለዋል።

