በአሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድ የሚመሩት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች ጋናዊው ሁለገብ ተጫዋች አስፈረሙ

ከቀናት በፊት የመሀል ተከላካዩ ጊትጋት ኩትን ያስፈረሙት እና በክረምቱ የዝውውር መስኮት ቡድናቸውን ለማጠናከር እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች አሁን ደግሞ በአማካይነት እና በተከላካይነት መሰለፍ የሚችለውን ጋናዊው ዴቪድ ኦፖንግ አፍራኔ የግላቸው አድርገዋል።
በቅርቡ ላለፉት ሦስት ዓመታት በተጫወተበት ኸርትስ ኦፍ ኦክ ውሉን ለማራዘም ካደረገው ያልተሳካ ድርድር በኋላ ስሙ ከተለያዩ የሀገሩ ክለቦች ጋር ሲያያዝ የነበረው ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም በኪንግ ፋይሰል እንዲሁም በጋና ከ23 ዓመት በታች መጫወት የቻለ ሲሆን አሁን ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመጫወት ከስምምነት ደርሷል።

