ቢጫዎቹ የአማካዩን ውል አራዘሙ

ቢጫዎቹ የአማካዩን ውል አራዘሙ

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት አጋማሽ ዳግም ወደ ወልዋሎ የተመለሰው አፈወርቅ ኃይሉ ውሉን አራዝሟል።

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የነበረውን ውል በስምምነት አፍርሶ ወደ ቀድሞ ክለቡ ወልዋሎ በማምራት ያለፉትን ስድስት ወራት ከቢጫዎቹ ጋር በማሳለፍ የኢትዮጵያ ዋንጫን ያነሳው አማካዩ አፈወርቅ ኃይሉ ለተጨማሪ ስድስት ወራት ውሉን አራዝሟል። በዓመቱ አጋማሽ ቡድኑን የተቀላቀለው እና ውሉ ላይ ቀሪ ስድስት ወራት የነበረው አማካዩ ዛሬ ተጨማሪ የስድስት ወራት ውል መፈረሙን ተከትሎ እስከ ቀጣይ የውድድር ዓመት መጨረሻ ከቢጫዎቹ ጋር ይቆያል። አፈወርቅ ከዚህ ቀደም በድሬ ፖሊስ ጨምሮ ወልዋሎ፣ ሀዲያ ሆሳዕና፣ ወልቂጤ ከተማ ባህር ዳር ከተማ እንዲሁም ዋናው እና የኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድንን ማገልገሉ ይታወሳል።