ከ30 ዓመታት በላይ በዐፄዎቹ ቤት ሲያገለግል የቆየው አሰልጣኝ አዳም ባዘዘው ወደ ነብሮቹ አምርቷል።

ከፋሲል ከነማ ጋር ከተጫዋችነት አንስቶ በተለያዩ ኃላፊነቶች ሲያገለግል የቆየው እና ከ2008 ጀምሮ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ በመሆን ሲሰራ የቆየው እንዲሁም በአጠቃለይ በክለቡ ያለፉትን 34 ዓመታት ቆይታ የነበረው አዳም ባዘዘው ለሀዲያ ሆሳዕና የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ለመሆን ተስማምቷል። አሰልጣኙ ከዚህ ቀደም በአዳማ ከተማ በተጫዋችነት እና በሕክምና ባለሙያነት ማገልገላቸውም ይታወቃል።
የፋሲል ከነማ የታማኝነት ምልክት በመሆን አይረሴ ጊዜያትን ያሳለፈው እና ከክለቡ ጋር የፕሪሚየር ሊጉን እንዲሁም የኢትዮጵያ ዋንጫን ጨምሮ ሌሎች ስኬቶችን ከክለቡ ጋር አብሮ ያሳካው አዳም አሁን ረጅም ዓመት ከሠራበት ዐፄዎቹ ቤት ተለያይቶ በሀዲያ ሆሳዕና ለቀጣዩ አንድ ዓመት የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ለመሆን ፊርማውን አኑሯል።

