የቻድ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ወደ አዲስ አዳጊው አመራ

የቻድ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ወደ አዲስ አዳጊው አመራ

በአሰልጣኝ ማቲዮስ ለማ የሚመራው ጋሞ ጨንቻ የቻድ ዜግነት ያለው ግብ ጠባቂ አስፈርሟል

ቀደም ብሎ ራሱን ለማጠናከር አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም የነባር ተጫዋቾች ውል ያራዘመው አዲስ አዳጊው ጋሞ ጨንቻ ግብ ጠባቂው ምባይናሰም ጆርዲንን አስፈርሟል። በተወለደበት ካሜሩን ሬንሰንስ ክለብ እግር ኳስን ጅማሮ ያደረገው ተጫዋቹ በመቀጠል በሌስ ኦስትሬስ ቆይታ አድርጎ ወደ ጋና ሊግ በማምራት በፋር ሬንጀርስ ለሁለት ዓመታት ተጫውቷል። ግብ ጠባቂው ወደ ሀገሩ ካሜሮን ተመልሶ ለኒው ስታርስ ፣ ለቀድሞ ክለቡ ሌስ አስትሬስ እና ለካነን ያውንዴ ተጫውቶ በካዛኪስታኑ ZSKA ዱሻንቤ እንዲሁም የተጠናቀቀውን ዓመት ደግሞ በደቡብ አፍሪካው ቬንዳ ቆይታን አድርጎ አሁን ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መጥቶ ለጋሞ ጨንቻ ለመጫወት ተስማምቷል።

1.93 ሜትር የሚረዝመው ግብ ጠባቂ በካሜሮን ቢወለድም ባለው የጥምር ዜግነት ምክንያት ለቻድ ብሔራዊ ቡድን እያገለገለ ይገኛል