የሴካፋ ዞን ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ውድድር ምድብ ድልድል ይፋ ሆነ

በአሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር የሚመራው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በሴካፋ ዞን ከ 20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ውድድር ላይ ተጋጣሚዎቹን አውቋል። ከደቂቃዎች በፊት ይፋ በሆነው ድልድልም ሀገራችን ኢትዮጵያ ታንዛንያ እንዲሁም ሩዋንዳ በሚገኙበት ምድብ 1 መደልደሏ ታውቋል።
በታንዛንያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው ሴካፋ ዞን ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ውድድር ላይ ለመሳተፍ 40 ተጫዋቾች በመጥራት ዝግጅት ከጀመረ በኋላ የስብስቡን ቁጥር ወደ 25 የቀነሰው ብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅቱን አጠናክሮ መቀጠሉ ይታወቃል።

