ቤኒናዊውን የአጥቂ አማካይ ወደ ፋሲል ከነማ ተቀላቀለ

በርከት ያሉ ዝውውሮችን እያደረጉ የሚገኙት እና የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በአዳማ ከተማ በማከናወን ላይ የሚገኙት ፋሲል ከነማዎች የቤኒን ዜግነት ያለውን የአጥቂ አማካይ እንዲሁም የመስመር ተጫዋች ሆኖ መጫወት የሚችለው ሮማሪክ ዲንሆ አሞውሱ እንዳስፈረሙ ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
ለሀገሩ ቤኒን ብሔራዊ ቡድን ተመርጦ በሞሮኮው አፍሪካ ዋንጫ ላይ የተሳተፈው ተጫዋቹ በሀገሩ ክለብ ኮተን ቆይታ ካደረገ በኋላ ባለፉት ሁለት ዓመታት ወደ ኮትዲቫር አቅንቶ በኤሴክ ሚሞሳስ ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ የቻለ ሲሆን አሁን ደግሞ ማረፊያውን ፋሲል ከነማ አድርጓል። ከአንድ ዓመት በፊት በ “Dîner de Gala du Football Ivoirien” በኮትዴቭዋር ሊግ በሚጫወቱ የውጪ ተጫዋቾች ዘርፍ ኮከብ ሆኖ የተሸለመው ተጫዋቹ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በይፋ ፌርማውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል።

