ተካልኝ ደጀኔ አዲስ ክለብ አግኝቷል

ተካልኝ ደጀኔ አዲስ ክለብ አግኝቷል

በሽረ ምድረ ገነት ቆይታ የነበረው የግራ መስመር ተከላካይ ወደ ሌላው የሊጉ ክለብ አመራ

የነባር ተጫዋቾች ውል አራዝመው አዳዲስ ተጫዋቾችም በማስፈረም በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለመሳተፍ ዝግጅት በማድረግ ላይ የሚገኙ በአሰልጣኝ ማቴዎስ ለማ የሚመሩት ጋሞ ጨንቻዎች አሁን ደግሞ የግራ መስመር ተከላካዩ ተካልኝ ደጀኔን አስፈርመዋል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሽረ ምድረ ገነት ቆይታ የነበረው ተካልኝ ከዚህ ቀደም በደደቢት፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ አርባምንጭ ከተማ፣ ኢትዮጵያ መድን እንዲሁም ፋሲል ከነማ መጫወት የቻለ ሲሆን አሁን ደግሞ ከሽረዎች ጋር ያለውን ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ማረፍያው ጋሞ ጨንቻ ሆኗል።