አዲስ አዳጊው ጋሞ ጨንቻ ቡድኑን ማጠናከሩን ገፍቶበታል።

የ2018 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ኮከብ አሰልጣኝነትን ክብርን ባገኘው በአሰልጣኝ ማቲዮስ ለማ የሚመሩት ጋሞ ጨንቻዎች ቅድመ ዝግጅታቸውን እያደረጉ ሲገኝ አሁን አጥቂው ያሬድ መኮንን ማስፈረማቸው ታውቋል።
ከአርባምንጭ ምድር የተገኘው እና ከሸገር ከተማ ጋር ያለፉትን ሁለት ዓመት ስኬታማ ቆይታ ያደረገው አጥቂው ያሬድ አሁን ወደ ጋሞ ጨንቻ ለመቀላቀል መስማማቱን አውቀናል።

