ቡድኑን በአዲስ መልክ ያጠናከሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከሁለት ተጫዋቾቹ ጋር በስምምነት ተለያይተዋል።

የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በቢሸፍቱ በክቡር ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ እያከናወነ የሚገኘው እና በዝውውሩ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ አዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ የቀላቀለው በሰርብያዊው አሰልጣኝ ሰርዲዮቪች ሚሉቲን ሚቾ የሚመራው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተከላካዩ ጥዑመልሳን ኃ/ ሚካኤል እና ከአማካዩ አበባየሁ ዮሐንስ ጋር በስምምነት መለያየቱ ታውቋል።
ሁለቱም ተጫዋቾች ቀሪ የአንድ ዓመት ውል እያላቸው በስምምነት መለያየታቸውም ታውቋል።

