አሰልጣኝ ማቲዮስ ለማ ረዳት አሰልጣኛቸውን ይፋ አድርገዋል።

በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ሲቢኢ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ የሚሆኑት ጋሞ ጨንቻዎች በቀጣይ ሳምንት የሊጉን ጨዋታ ከመጀመራቸው አስቀድሞ ዋና አሰልጣኙ ማቲዮስ ለማ ረዳት አሰልጣኛቸው እንዲሆን አብርሃም መላኩን መሾማቸው ታውቋል።
አሰልጣኝ አብርሃም መላኩ ከዚህ ቀደም በዋና እና ረዳት አሰልጣኝነት ባህር ዳር ከተማ፣ እንዲሁም ዋና አሰልጣኝ በመሆን በአውስኮድ ፣ ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን፣ ደብረ ማርቆሰ፣ እንጅባራ እና ባሳለፍነው ዓመት ቤንች ማጂ ቡና የሰሩ ሲሆን አሁን አዲስ አዳጊዎቹን በረዳት አሰልጣኝነት ለማገልገል መሾማቸውን አውቀናል።

