አሰልጣኝ ካሊድ መሐመድ ረዳት አሰልጣኛቸውን ይፋ አድርገዋል

በአሰልጣኝ ካሊድ መሐመድ የሚመሩት አዲስ አዳጊዎቹ ሀላባ ከነማዎች በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ለሚሳተፉበት የሲቢኢ ፕሪምየር ሊግ እራሳቸውን በማጠናከር ዝግጅታቸውን በመስራት እንደሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን አሁን ደግሞ አሰልጣኝ የኔነህ ንጋቱን በረዳት አሰልጣኝነት ሾመዋል።
አሰልጣኝ የኔነህ ንጋቱ ከዚህ ቀደም በሴቶች እግርኳስ በአዲስ አበባ ከተማ በዋና አሰልጣኝነት ጠንካራ ስራ መስራቱ የሚታወስ ሲሆን ከዚህ በተጫማሪም በአዲስ አበባ ከተማ ከ20 ዓመት በታች የወንዶች ቡድን፣ በሱሉልታ ከተማ፣ ቢሾፍቱ ከተማ፣ መተሀራ ስኳር፣ ጅማ ከተማ፣ ጨፌ ዶንሳ እንዲሁም በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በአንደኛ ሊግ ሮቤ ከተማን ማሰልጠን የቻለ ባለ ብዙ ልምድ አሰልጣኝ ነው።

