የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞዞምቢክ አቻው ጋር የሚያደርገው የዓርቡ ወሳኝ አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ፍልሚያ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ሽፋት እንደሚያገኝ ለማጣራት ሞክረናል።
የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ የምድብ 3ኛ ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ መደረግ የሚጀምሩ ሲሆን 48 ሀገራት በኬንያ፣ ታንዛኒያ እና ዩጋንዳ በሚካሄደው የአህጉሪቱ ትልቁ ውድድር ላይ ለሚያሳትፉ 24 ቦታዎች ፉክክራቸውን ይጀምራሉ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም የምድብ 3ኛ ጨዋታውን ከሞዛምቢክ አቻው ጋር ለማከናወን በትናንትናው ዕለት ወደ ማፑቶ ያመራ ሲሆን ጨዋታውንም ከነገ በስትያ ዓርብ 10 ሰዓት ያከናውናል። ታዲያ ይህ ወሳኝ ጨዋታ የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ሽፋን እንደሚያገኝ ለማጣራት ሞክረናል።

ሶከር ኢትዮጵያ ባደረገችው ማጣራት ይህ ጨዋታ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ሽፋን የሚያገኝ ሲሆን ጨዋታውንም በሀገራችን ስርጭቱን የማስተላለፍ መብት ያለው ሱፐር ስፖርት በ227 ቻነሉ እንደሚያስተላልፍ አውቀናል።
እንደ ዝግጅት ክፍላችን መረጃ ከሆነ ከሱፐር ስፖርት በተጨማሪ አንድ የሀገራችን ግዙፍ የቴሌቪዥን ተቋም ይህንን ጨዋታ ለማስተላለፍ መብቱን ለመግዛት ድርድር ላይ መሆኑን አውቀናል። ምናልባት ድርድሩ በጥሩ ሁኔታ የሚያልቅ ከሆነ ይህ የሀገራችን ተቋም ለሀገር ቤት ተመልካቾች በነፃ ጨዋታውን ተደራሽ የሚያደርግ ይሆናል።

