የሉሲዎቹ አለቃ ለ25 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል

የሉሲዎቹ አለቃ ለ25 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ ለአምስት ቀናት ካምፒንግ ለ25 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል።

በ2028 የሎስ አንጀለስ ኦሊምፒክ ማጣርያ ሩዋንዳን በድምር ውጤት አሸንፎ ወደ ተከታይ ዙር ያለፈው ብሔራዊ ቡድናችን በመጋቢት ወር ከታንዛንያ ጋር ወሳኝ የ3ኛ ዙር ጨዋታ የሚያከናውን ሲሆን የቡድኑ አሰልጣኝ ቻለው ለሜቻም ለ25 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ከቅዳሜ ጀምሮ ለአምስት ቀናት ካምፒንግ እንደሚኖር ተገልፀል።

የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ውድድር በሴቶች የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች ምክንያት በዚህ ሳምንት የማይካሄድ ሲሆን ብሔራዊ ቡድኑ በሚኖረው ካምፒንግ ወቅት የወዳጅነት ጨዋታ ከሌሎች ብሔራዊ ቡድኖች ጋር ስለማድረጉ ግን ፌዴሬሽኑ አልጠቀሰም።

የ25 ተጫዋቾች ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች

ቤተልሔም ዮሐንስ (መቻል)፣ ፎዚያ ዝናቡ (ሸገር ከተማ)፣ ሊንጎ ኡማን (ቦሌ ክ/ከተማ)፣ ንግሥት መዓዛ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)

ተከላካዮች

ብዙዓየሁ ታደሰ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ነፃነት ጸጋዬ (መቻል)፣ ታሪኳ ዴቤሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ እጸገነት ብዙነህ (መቻል)፣ ሀሳቤ ሙሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ብርቄ አማረ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ቤተልሔም በቀለ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ትርሲት ወንድወሰን (ቦሌ ክ/ከተማ)

አማካዮች

ዙፋን ደፈርሻ (መቻል)፣ ኒቦኝ የን (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ሃና ሲሳይ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ቤተልሔም መንተሎ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ እፀገነት ግርማ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ጋብርኤላ አበበ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)

አጥቂዎች

አረጋሽ ካልሳ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ቱሪስት ለማ (መቻል)፣ እሙሽ ዳንኤል (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ዳግማዊት ሰለሞን (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ሲርያ ተሾመ (ጉለሌ ክ/ከተማ)፣ ምትኬ ብርሀኑ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ምህረት አየለ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)