ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ አርባምንጭ ከተማ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ኢትዮ ኤሌክትሪክ1-1አርባምንጭ ከተማ

17′ ፍፁም ገብረማርያም | 44′ ገብረሚካኤል ያዕቆብ

 

ተጠናቀቀ!!!

ጨዋታው 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።



90+1′ የተጫዋች ለውጥ – አርባምንጭ ከተማ

አመለ ሚልክያስ ወጥቶ ተመስገን ዱባ ገብቷል።


90′ ተጨማሪ ሰዓት – 4 ደቂቃ


88′ አማኑኤል ጎበና የዳኛን ውሳኔ በመቃወሙ የማስጠንቀቂያ ካርድ አይቷል።


80′ አለምነህ የመታው የቅጣት ምት በግቡ በግራ በኩል ወጥቷል።


79′ ተካልኝ ደጀኔ በተስፋዬ ላይ በሰራው ጥፋት ቢጫ ካርድ አይቷል።


77′ በረከት ቦጋለ በኢብራሂም ፎፋኖ ላይ በሰራው ጥፋት ምክኒያት ቢጫ ካርድ ተሰጥቶታል።


67′ 4ተኛው  ዳኛ በጨዋታው በቀይ የወጣው ዳዊት እስጢፋኖስ ከተቀያሪ ተጫዋቾች ወንበር ላይ ተነስቶ ወደውስጥ እንዲገባ አድርገዋል።


66′ የተጫዋች ለውጥ – አርባምንጭ ከተማ

ገብረሚካኤል ያዕቆብ ወጥቶ ተሾመ ታደሰ ገብቷል።


64′ የተጫዋች ለውጥ – ኤሌክትሪክ

ፍፁም ገብረማርያም  ወጥቶ ብሩክ አየለ ገብቷል።


61′ ሙሉአለም ጥላሁን ቅሬታውን በአግባቡ ባለማቅረቡ ቢጫ ካርድ አይቷል።


56′ የተጫዋች ለውጥ – አርባምንጭ ከተማ

ወንደወሰን ሚልኪያስ ወጥቶ በረከት ቦጋለ ገብቷል።


49′ ቀይካርድ!

ዳዊት እስጢፋኖስ በምንተስኖት ላይ በሰራው ጥፋት ቢጫ ሲሰጠው ውሳኔውን በፀጋ ባለመቀበሉ በሁለተኛ ቢጫ ከሜዳ ተወግዷል።


48′ ወንድሜነህ ዘሪሁን ከርቀት የመታው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል።


ተጀመረ!

46′ ሁለተኛው አጋማሽ በአርባምንጭ አማካኝነት ተጀምሯል።



ዕረፍት!!!

የመጀመሪያው አጋማሽ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።


45+1′ ገብረሚካኤል ያዕቆብ ሰዓት አባከንክ በሚል የመጀመሪያውን ቢጫ አይቷል።


45′ ተጨማሪ ሰዓት 2 ደቂቃ


44′ ጎልልል!!! አርባምንጭ!

ገብረሚካኤል ያዕቆብ ከአመለ ሚልኪያስ ጋር በጥሩ ቅብብል ካለፈ በኀላ ከሳጥኑ ውጪ አክርሮ በመምታት አርባምንጭን አቻ አድርጓል።


35′ ጨዋታው በዳኛው ፊሽካ ምክንያት በተደጋጋሚ እየተቆራረጠ ይገኛል።


26′ ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ያገኙትን ሁለተኛ ግብ መሆን የሚችል ኳስ ኢብራሂም ፎፋኖ አግኝቶ ተካልኝ ደጀኔ ተንሸራቶ በመግባት አምክኖታል።


17′ ጎልልል!!! ኤሌክትሪክ

ሙሉአለም ጥላሁን ያሻማውን ኳስ ግብ ጠባቂው ሲተፋው ተመስገን ካስትሮ ተቀብሎ ለማውጣት ሲሞክር ፍፁም ገብረማርያም ተደርቦ የመጀመሪያውን ግብ አስቆጥሯል።


10′ ፍፁም ገብረማርያም ከግብ ጠባቂው ጋር ተገናኝቶ ከመምታቱ በፊት ወግደረስ አበበ ተንሸራቶ አውጥቶበታል።


5′ ጨዋታው በተቀዛቀዘ ሁኔታ ቀጥሏል።


1′ ጨዋታው በኤሌክትሪክ አማካኝነት ተጀምሯል።


ከ1977 እስከ 1981 ድረስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለተጫወተው እና በዚህ ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት ለተለየው ዘላለም ተሾመ የ1 ደቂቃ የህሊና ፀሎት ተደርጓል።


አሰላለፍ – ኤሌክትሪክ (4-3-3)

22. ሱሊማን አቡባካር

11. አወት ገ/ሚካኤል– 5. አዲስ ነጋሽ–15. ተስፋዬ መላኩ —  7. አለምነህ ግርማ

23. አሸናፊ ሽብሩ — 24. ዋለልኝ ገብሬ– 10. ዳዊት እስጢፋኖስ

16. ፍፁም ገ/ማርያም — 18. ሙሉአለም ጥላሁን —  4. ፎፋኖ ኢብራሂም

ተጠባባቂዎች

1. ኦኛ ኦሞኛ

19. ደረጄ ሀይሉ

14. ስንታየው ሠለሞን

8. በሀይሉ ተሻገር

9. ብሩክ አየለ

17. አብዱልሐኪም ሱልጣን

13. ትዕዛዙ መንግስቱ


አሰላለፍ – አርባምንጭ (4-4-2)

99 ጃክሰን ፊጣ

2 ተካልኝ ደጀኔ — 15 ተመስገን ካስትሮ — 20 ወንደሠን ሚልኪያስ — 14 ወግደርስ  አበበ

10 ወንድሜነህ ዘሪሁን — 4 ምንተስኖት አበራ — 8 አማኑኤል ጎበና –17 ታደለ መንገሻ

12 አመለ ሚልኪያስ — 19 ገብረሚካኤል ያዕቆብ

ተጠባባቂዎች

1 አንተነህ መሳ

3 ታገል አበበ

24 በረከት ቦጋለ

25 አለልኝ አዘነ

18 አስጨናቂ ፀጋዬ

23 ተሾመ ታደሠ

11 ተመስገን ዱባ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *