FTቅዱስ ጊዮርጊስ 1-0ወልድያ
ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል።
90′ ተጨማሪ ሰዐት – 3 ደቂቃ
89′ የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
አቡበከር ሳኒ ወጥቶ ናትናኤል ዘለቀ ገብቷል።
86′ ወልዲያዎች ደጉ ደበበ ያቀበለውን ኳስ ግብጠባቂው ፍሬው በእጁ በመያዙ ያገኙትን የሁለተኛ ቅጣትምት መጠቀም አልቻሉም።
84′ የተጫዋች ለውጥ – ወልዲያ
ቢንያም ዳርሰማ ወጥቶ ነጋ በላይ ገብቷል።
82′ ራምኬል ሎክ ከግራ መስመር ያሻገረውን ኳስ አዳነ ግርማ ሞክሮት ወደውጪ ወጥቶበታል።
80′ የተጫዋች ለውጥ – ወልዲያ
ዳንኤል ደምሴ ወጥቶ ታዬ አስማረ ገብቷል።
79′ አንዱአለም ንጉሴ ጫላ በግንባሩ ያቀበለውን ኳስ መትቶ ፍሬው መልሶበታል።
75′ ጎል!!!!
አቡበከር ሳኒ ከሳላህዲን የተቀበለውን ኳስ ከሳጥኑ ጠርዝ ላይ በቀጥታ ወደግብ በመምታት አስቆጥሮ ቅዱስ ጊዮርጊስን መሪ አድርጓል።
73′ የተጫዋች ለውጥ – ወልዲያ
በድሩ ኑርሁሴን ወጥቶ ጫላ ድሪባ ገብቷል።
69′ አበባው ቡጣቆ ያሻማውን ቅጣት ምት ሳላህዲን በግንባሩ ቢሞክርም ኳሱ ዒላማውን አልጠበቀም።
61′ አበባው ቡጣቆ ከግቡ 30 ሜትር ርቀት ላይ የመታው ቅጣት ምት ወደውጪ ወጥቷል።
60′ ሀብታሙ ሸዋለም ቅዱስ ጊዮርጊሶች ያገኙትን ቅጣት ምት ሊመቱ ሲሉ ዳኛው ካስቀመጡት ቦታ በመልቀቁ ቢጫ ካርድ አይቷል።
58′ የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ያስር ሙገሬዋ ወጥቶ ሳላህዲን ሰዒድ ገብቷል።
57′ የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ዘካርያስ ቱጂ ወጥቶ ራምኬል ሎክ ገብቷል።
53′ አብዱልከሪም ንኪማ ወደ አደጋ ክልሉ የተሻማውን ኳስ ከግቡ በቅርብ ርቀት አግኝቶ ቢመታም ወደውጪ ወጥቶበታል።
48′ አዳነ ግርማ አበባው ያሻማውን የማዕዘን ምት አግኝቶ ቢሞክርም የወልዲያ ተከላካዮች ተደርበው መልሰውታል።
46′ ሁለተኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀምሯል።
የመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ ያለግብ አቻ ተጠናቋል።
45+1′ ምንተስኖት አዳነ ፍሬዘር ቀኝ መስመር ያሻገረውን ኳስ አግኝቶ ቢመታም ወደውጪ ወጥቶበታል።
45′ ተጨማሪ ሰዐት – 1 ደቂቃ
39′ ሀብታሙ ሸዋለም ኳሱን ከአቡበከር በመቀማት ወደግብ ቢመታም ግብጠባቂው ፍሬው ይዞበታል።
34′ አንዱአለም ንጉሴ ከሀብታሙ ሸዋለም የተቀበለውን ጥሩ ኳስ ወደግብ ቢሞክርም ኳሱ ዒላማውን ሳይጠብቅ ቀርቷል።
33′ አብዱልከሪም ንኪማ በግንባሩ ግብ ቢያስቆጥርም ከጨዋታ ውጪ አቋቋም ላይ ስለነበር ግቡ ተሽሯል።
27′ ፍሬዘር ካሳ ምንያህል ይመርን ጎትቶ በመጣል ጥፋት በመስራቱ የጨዋታውን የመጀመሪያ ቢጫ ካርድ አይቷል።
23′ ወልዲያዎች በመልሶ ማጥቃት ያገኙትን ዕድል ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊስ ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
20′ ያስር ሙገሬዋ ከ30 ሜትር ርቀት አካባቢ የመታው ኳስ ከግቡ አናት በላይ ወጥቷል።
15′ አንዱአለም ንጉሴ ከርቀት የመታውን ኳስ ግብጠባቂው ፍሬው ይዞታል።
14′ በድሩ ኑርሁሴን የመታውን ኳስ ደጉ በሳጥኑ ውስጥ በእጁ መልሶታል ብለው ወልዲያዎች ቅሬታ ቢያሰሙም ዳኛው ጨዋታውን አስቀጥለዋል።
9′ አቡበከር ሳኒ ኳስ ይዞ ወደሳጥኑ ሲገባ በአዳሙ መሐመድ ተጠልፌያለሁ ብሎ ቢወድቅም ዳኛው በዝምታ አልፈዋል።
6′ አንዱአለም ንጉሴ ከሳጥኑ ውጪ ወደግብ የመታው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል።
1′ አብዱልከሪም ንኪማ ከመስመር ወደ አደጋ ክልሉ የላከውን ኳስ ያሬድ ዘውድነህ አውጥቶታል።
1′ ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ አማካኝነት ተጀምሯል።
የመጀመሪያ አሰላለፍ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
1 ፍሬው ጌትነት
2 – ፍሬዘር ካሳ – 15 አስቻለው ታመነ – 12 ደጉ ደበበ (አምበል) – 4 አበባዉ ቡጣቆ
27 – ያስር ሙገሬዋ – 23 ምንተስኖት አዳነ – 27 አብዱልከሪም ኒኪማ
20 ዘካሪያስ ቱጂ – 19 አዳነ ግርማ – 18 አቡበከር ሳኒ
ተጠባባቂዎች
22 ዘሪሁን ታደለ
3 መሀሪ መና
13 ሳላሀዲን ባርጊቾ
25 አንዳርጋቸው ይላቅ
10 ራምኬል ሎክ
7 ሳላህዲን ሰዒድ
26 ናትናኤል ዘለቀ
የመጀመሪያ አሠላለፍ – ወልድያ ከተማ
16 ኤሚክሪል ቢሌንጌ
3 ቢኒያም ዳርሰማ — 14 ያሬድ ዘውድነህ — 25 አዳሙ መሀመድ — 6 ዮሐንስ ሀይሉ
23 ሙሉጌታ ወ/ጊዮርጊስ — 18 ዳንኤል ደምሴ — 21 ሀብታሙ ሸዋአለም— 8 ምንያህል ይመር
11 በድሩ ኑርሁሴን — 2 አንዱአለም ንጉሴ
ተጠባባቂዎች
64 ዳዊት አሰፋ
15 ጫላ ድሪባ
4 ሙሉነህ ጌታሁን
28 ታዬ አስማረ
10 ሙሉጌታ ረጋሳ
19 አለማየው ግርማ
20 ነጋ በላይ