FT ቅዱስ ጊዮርጊስ 2-0 ኤሲ ሊዮፓርድስ
16′ 90+1 ሳላዲን ሰይድ
ድምር ውጤት ፡ 3-0
የቅዱስ ጊዮርጊስ ታሪካዊ ድል በዚህ መልኩ ተጠናቋል !
ተጨዋቾቹ እና የክለቡ የበላይ ጠባቂ አቶ አብነት ገ/መስቀል ጭምር ሜዳ ውስጥ ደስታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ ! ደጋፊው በሙሉ ስታድየሙ ከፍተኛ ደስታ ላይ ይገኛል !
ተጠናቀቀ !!!!!!!! ቅዱስ ጊዮርጊስ የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ውድድርን ተቀላቀለ !!!!!
90+1 ጎል ቅዱስ ጊዮርጊስ ! ሳላዲን ሰይድ
ግብ ጠባቂው የማዕዘን ምት ለመሻማት በሄደበት ሳላዲን ሰይድ በመልሶ ማጥቃት ከመሀል ሜዳ ጀምሮ ይዞ በመሄድ ግብ አስቆጥሯል
90′ ጭማሪ ደቂቃ 2 !
88′ የተጨዋች ለውጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ያስር ሙገርዋ ግብቶ አዳነ ግርማ ወጥቷል
87′ ባጎዮካ በግምት ከ 25 ሜትር የመታው የቅጣት ምት ወደውጪ ወጥቷል ።
85′ ሊዮፓርድሶች በዛ ያሉ ተጨዋቾችን የማጥቃት ወረዳው ላይ ለማሳተፍ እየሞከሩ ነው ። ጊዮርጊሶችም አልፎ አልፎ የመልሶ ማጥቃት እድሎችን እያገኙ ነው ። ሁለቱም ቡድኖች ግን ያለቀለት የግብ እድል መፍጠር አልቻሉም ። ጨዋታው እንደተቀዛቀዘ ነው ።
81 ‘ የተጨዋች ለውጥ ኤሲ ሊዮፓርድስ
ያኒክ ምብማማ ገብቶ ማቮንጎ ቺሊንጎ ወጥቷል
78′ የተጨዋች ቅያሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ
አቡበከር ሳኒ በሀይሉ አሰፋን ተክቶ ገብቷል
76′ ቺምባምባ ብዙ የጊዮርጊስ ተጫዋቾችን በግል ብቃቱ አልፎ ከቅርብ ርቀት የሞከረው ኳስ ወደውጪ ለጥቂት ወጣ ። ለግብ የቀረበ ከባድ ሙከራ !
72′ ጨዋታው በጣሙን ተቀዛቅዟል ፈረሰኞቹ የግብ ሙከራ ከማድረግ ተቆጥበዋል ። ከካደረጉት ቅያሪ አንፃርም ውጤት ወደማስጠበቁ ያደሉ ይመስላሉ ።
70′ ሳላዲን ባርጌቾ ምቤንዛ ላይ በሰራው ጥፋት የቢጫ ካርድ ተመልክቷል ።
68 ‘ የተጨዋች ቅያሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ተስፋዬ አለባቸው ገብቶ አብዱልከሪም ኒኪማ ወጥቷል ።
65 ‘የተጨዋች ቅያሪ ኤሲ ሊዮፓርድስ
ሳሙ ሺምባምባ በአማካዩ ንቴላ ካሌማ ተተክቷል ።
62′ የፈረሰኞቹ ተጨዋቾች የመስመር አጥቂዎቹን ጨምሮ ከኳስ ጀርባ ሚገኙበት አጋጣሚ እየበዛ ነው ። የሚገኙ ኳሶችንም ለሳላዲን ለማድረስ እየጣሩ ይገኛሉ ።
59′ እንግዳው ቡድን ከመጀመሪያው ግማሽ የተሻለ ወደግብ እየደረሰ ይገኛል ። አሁንም ጆቫያል ቫሬል ናትናኤል በግንባሩ ያወጣውን ኳስ አግኝቶ በቀጥታ ሲሞክር ለጥቂት ወደላይ ወጥቶበታል ።
57′ የግራ መስመር ተከላካዩዲሚትሪ ቢሲኪ ያሻማውን ኳስ አጥቂው ጋይ ምቤንዛ በግንባሩ ሞክሮ ወደላይ ተነስቶበታል ።
55′ የቅስዱ ጊዮርጊስ ተከላካዮች በአግባቡ ያላወጡትን ኳስ ጁኒየር ሞዚታ አግኝቶ ከቅርብ ርቀት ሲሞክር ሮበርት ተደርቦ አድኖበታል ።
52′ አምበሉ ኒጎንጋ በሁለት እግሩ ፕሪንስ ላይ ሸርተቴ በመውረዱ የጨዋታውን የመጀመሪያ ቢጫ ካርድ ተመልክቷል ።
51’አበባው ከመሀል ሜዳ ግራ መስመር ላይ ያሻማውን ኳስ ነፃ የነበረው አዳነ በግንባሩ ሞክሮ ወደላይ ተነስቶበታል ።
48 ‘የተጨዋች ቅያሪ ኤሲ ሊዮፓርድስ
ሴዛር ጋንዜ ገብቶ የመስመር አማካዩ ጁኒየር ኮኔ ወጥቷል
46′ ሁለተኛው አጋማሽ በጋይ ምቤንዛ አማካይነት ተጀመረ ።
የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቀቀ !
45 ‘ ሳላዲን በፈጣን መልሶ ማጥቃት ወደውስጥ መሬት ለመሬት ኳስ ቢልክም በሀይሉ መድረስ አልቻለም። ባዶ ጎል ነበር !
45′ ጭማሪ ደቂቃ !
43′ በስቴድየሙ መጠነኛ ካፍያ እየጣለ ይገኛል ።
40′ አስቻለው ታመነ ኳሶችን ከማስጣል ጀምሮ ወደፊት ገፍቶ ጥቃትን እስከማስጀመር ድረስ በጥሩ ሁኔታ እየንተቀሳቀሰ ይገኛል ።
39′ የፊት አጥቂው ጋይ ምቤንዛ የመጀመሪያ ሙከራ አድርጓል ። ከመስመር የተላከለትን ኳስ በመጠቀም ሳላዲን ባርጌቾን አልፎ ሲሞክር ኳስ ወደላይ ወጥታለች ።
37′ ሊዮፓርድሶች እስካሁን ይህ ነው የሚባል የግብ እድል መፍጠር አልችቻሉም ።
35′ ፕሪንስ ከቀኝ መስመር ላይ መሬት ለመሬት የላከውን ድንቅ ኳስ አዳነ ከቅርብ ርቀት ሞክሮ ወደላይ ወጥቶበታል ።
33′ ጊዮርጊሶች በመልሶ ማጥቃት በፈጠሩት ዕድል ፕሪንስ በግብጠባቂው አናት ላይ በግንባሩ ያሳለፈው ኳስ ገባ ሲባል የመሀል ተከላካዩ ኒጎንጋ አውጥቶታል ። ጨዋታው በማዕዘን ምት ቀጥሏል ።
30′ እንግዳው ቡድን ኳስ ይዞ ወደፊት ለመሄድ ይሞክር እንጂ ኳስ በሚነጠቅበት ወቅት ተጨዋቾቹ ወደመከላከል የሚያደርጉት ሽግግር ፍጥነቱ ዝግ ያለ ነው ። ፈረሰኞቹ የማጥቃት ፍጥነታቸውን መጨመር ከቻሉ በርካታ የግብ ዕድሎችን ለማግኘት የሚችሉበት አጋጣሚ ይኖራል ።
29′ አዳነ ግርማ ከሳላዲን ሰይድ የተቀበለውን ኳስ ከግራ መስመር ጠርዝ ላይ ከርቀት አክርሮ ሞክሮ ወደላይ ወጥቶበታል ።
25′ ሊዮ ፓርድሶች ሙሉ ለሙሉ በፈረሰኞቹ ሜዳ ላይ ሆነው የግብ እድል ለመፍጠር እየሞከሩ ነው ሆኖም የጊዮርጊሶች የተከላካይ መስመር እስካሁን ምንም እድል አልሰጣቸውም ።
22′ በሀይሉ አሰፋ ከግቡ ቅርብ ርቀት ላይ ለሳላዲን አቀብሎት ሳላዲን ያስቆጠረው ኳስ ከጨዋታ ውጪ ሆኗል ።
20′ ጊዮርጊሶች እስካሁን የሊዮፓርድስን የቆሙ ኳሶች በሚገባ እያመከኑ እና በጨዋታ እንቅስቃሴም የተጋጣሚያቸውን ጫና በቀላሉ እያከሰሙ ይገኛሉ ።
19’በሀይሉ አሰፋ ከቀኝ መስመር ያሻማውን ኳስ ሳላዲን በግንባሩ ሞክሮ የግንቡ የግራ ቋሚ መልሶበታል ። የሚያስቆጭ አጋጣሚ !
18′ ጊዮርጊሶች በመልሶ ማጥቃት ይዘው የገቡትን ኳስ ኒኪማ ከሳላዲን ተቀብሎ ሲሞክር በጥቂቱ ወደላይ ተነስቶበታል ።
16′ ጎል ቅዱስ ጊዮርጊስ! ሳላዲን ሰይድ !
ግብ ጠባቂው ሉቱኑ በረጅሙ ሊለጋው የነበረውን ኳስ ሳላዲን ተደርቦ አስቆጥሯል !
10′ ሊዮ ፓርድሶች ኳስ ይዘው በቅዱስ ጊዮርጊስ ሜዳ ላይ ለመግባት እየሞከሩ ነው ። ጊዮርጊስ የመልሶ ማጥቃት እድሎችን ለመፍጠር እየሞከረ ነው ። ጨዋታው ቀዝቀዝ ብሏል ።
5′ ሊዮፓርድሶች በጨዋታው የመጀመሪያው ደቂቃዎች ላይ ወደፊት ገፍተው ለመጫወት ያሰቡ ይመስላሉ ።
3′ ናትናኤል ዘለቀ ከግራመስመር ያሻማትን ኳስ በሀይሉ ሳይደርስባት ለትቂት ወጥታለች ።
1’ ጁኒየር ሞዚታ ከግራ መስመር ሳጥን ጠርዝ ላይ የሞከረው ኳስ ወደላይ ተነስቷል ።
1’ጨዋታው በሳልሀዲን ሰይድ አማካይነት ተጀመረ ።
09፡55 በመጀመሪያው ግማሽ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከዳፍ ወደ ምስማር ተራ ሊዮ ፓርድስ ደግሞ ከምስማር ተራ ወደ ዳፍ ያጠቃሉ ።
09፡50 የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾች በተለመደው የቀይ እና የብርቱካናማ እንዲሁም ሊዮፓርድሶች በሙሉ የአረንጓዴ መለያዎች ወደሜዳ ገብተዋል ። የክብር እንግዶች ከተጨዋቾች ጋር እየተዋወቁ ይገኛሉ ።
09፡45 የአዲስ አበባ ስታድየም ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ በደጋፊዎች ተሞልቷል ።
09 ፡40 የሁለቱም ቡድኖች ተጨዋቾች አሟሙቀው በመጨረስ ወደ መልበሻ ክፍል ገብተዋል ።
የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ
30 ሮበርት ኦዶንካራ
2 ፍሬዘር ካሳ – 15 አስቻለው ታመነ – 13 ሳላዲን በርጊቾ – 4 አበባው ቡታቆ
27 አብዱልከሪም ኒኪማ – 26 ናትናኤል ዘለቀ – 19 አዳነ ግርማ (አምበል)
16 በሀይሉ አሰፋ – 7 ሳላዲን ሰኢድ – 11 ፕሪንስ ሲቬሪንሆ
ተጠባባቂዎች
22 ዘሪሁን ታደለ
3 መሀሪ መና
12 ደጉ ደበበ
18 አቡበከር ሳኒ
21 ተስፋዬ አለባቸው
24 ያስር ሙገርዋ
17 ብሩኖ ኮኔ
የኤሲ ሊዮፓርድስ አሰላለፍ
1 ሉቱኑ ዱሌ
29 ጆቫያል ቫሬ – 5 ቲልተን ንጎንጋ (አምበል) – 15 ሌዶን ኤፓኮ – 6 ዲሚትሪ ቢሲኪ
10 ንቴላ ካሌማ – 8 አሉ ባጋዮኮ
22 ጁንየር ኮኔ – 7 ማቮንጎ ቺሊምቦ – 28 ጁንየር ሞዚታ
7 ጋይ ምቤንዛ
ተጠባባቂዎች
16 ትሬዘር ኢሌንጋ
26 ካሮፍ ባካዋ
23 ዱዋ አንኪራ
19 ቻርዲን ማዲላ
13 ሳሙ ሺምባምባ
20 ያኒክ ምቤማ
12 ሴዛር ጋንዜ
09፡ 30 በመቀጠል የቡድኖቹን አሰላለፍ ይዘን እንመለሳለን ።
09 ፡ 10 የሁለቱ ቡድኖች ተጨዋቾች ሰውነታቸውን ለማሟሟቅ ወደሜዳ ገብተዋል ።
09፡00 የስታድየሙ አብዛኛው ቦታዎች በቅዱስ ጊዮርጊስ መለያ ባሸበረቁ እና የክለቡ ምልክት የሆነው የV ምስል ያረፈባቸውን ባንዲራዎች በያዙ ደጋፊዎች እየተሞሉ ይገኛሉ ።
08፡50 ዳኞች የሜዳውን ዝግጁነት ፈትሸው ወደመልበሻ ክፍል ገብተዋል ።
08፡40 የኤሲ ሊዮፓርድስ ቡድን አባላት ወደ ስታድየሙ እየገቡ ይገኛሉ ።
08 ፡ 30 የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾች ወደ አዲስ አበባ ስታድየም ደርሰዋል ። ደጋፊውም በዝማሬ ተቀብሏቸዋል ።
ዳኞች
ጨዋታውን የሚመሩት አራቱም ዳኞች ከሱማልያ ሲሆኑ ኮሚሽነሩ ከሱዳን ናቸው፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስ ግምታዊ አሰላለፍ
ሮበርት ኦዶንካራ
ፍሬዘር ካሳ – አስቻለው ታመነ – ሳላዲን በርጊቾ – አበባው ቡታቆ
አብዱልከሪም ኒኪማ – ናትናኤል ዘለቀ – አዳነ ግርማ
በሀይሉ አሰፋ – ሳላዲን ሰኢድ – ፕሪንስ ሲቬሪንሆ
የመጀመርያ ጨዋታ
ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጀመርያው ጨዋታ ወደ ዶሊሴ አምርቶ በምንተስኖት አዳነ ግብ 1-0 በማሸነፍ አንድ እግሩን ወደ ምድብ ድልድሉ ማስገባት ችሏል፡፡ በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ የምድብ ድልድል ውስጥ ለመግባትም በእጅጉ ተቃርቧል፡፡
የመጡበት መንገድ
ቅዱስ ጊዮርጊስ በቅድመ ማጣርያው የሲሸልሱን ኮት ዲኦር 5-0 በሆነ ድምር ውጤት አሸንፎ ወደ ተከታዩ ዙር ሲያልፍ ኤሲ ሊዮፓርድስ የካሜሩኑ ዩእምኤስ ደሉምን በድምሩ 2-1 አሸንፎ ማለፍ ችሏል፡፡
ሰላም ክቡራት እና ክቡራን !
የ2017 ካፍ ቶታል ቻምፒየንስ ሊግ አንደኛ ዙር የመልስ ጨዋታዎች ከአርብ ጀምሮ እየተካሄዱ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኮንጎ ሪፐብሊኩ ኤሲ ሊዮፓርድስ ደ ዶሊሴ ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ስታድየም የሚያደርጉት ጨዋታም 10:00 ላይ ይካሄዳል፡፡ ሶከር ኢትዮጵያ የጨዋታውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል፡፡
መልካም ውሎ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር!