ሦስት ክለቦች የዲሲፕሊን ቅጣት ተላልፎባቸዋል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
ሀዲያ ሆሳዕና፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ወላይታ ድቻ ደጋፊዎቻቸው በፈፀሙት ያልተገባ ድርጊት ምክንያት ከፍተኛ የገንዘብ መቀጮ ተጥሎባቸዋል።

የፕሪምየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ 11ኛ የጨዋታ ሳምንት መጠናቀቅን ተከትሎ ከጨዋታ አመራሮች የቀረቡ ሪፖርቶችኖ ተንተርሶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ሀዲያ ሆሳዕና በጅማ አባጅፋር 4-2 በተሸነፈበት ጨዋታ የሀዲያ ሆሳዕና ጨዋታውን የመራው አርቢትርን አፀያፊ ስድብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት የቀረበባቸው ሲሆን በተመሳሳይ ወላይታ ድቻ አዲስ አበባ ከተማን በረታበት ጨዋታ የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች አርቢትሩን በተመሳሳይ አፀያፊ ስድቦችን ስለመስደባቸው ሪፖርት መቅረቡን ተከትሎ ከዚህ ቀደም የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ታሳቢ በማድረግ ሁለቱም ቡድኖች እያንዳንዳቸው የ75,000 ብር ቅጣት ተጥሎባቸዋል።

በተያያዘም የድሬዳዋ ከተማ ደጋፊዎች ቡድናቸው በሀዋሳ በተሸነፈበት ጨዋታ ዳኛን በመዝለፋቸው እንዲሁ የ50,000 ብር ቅጣት ተጥሎባቸዋል።

በሌሎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ደግሞ አርባምንጭ ከሲዳማ አቻ በተለያየበት ጨዋታ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ የተወገደው ሀቢብ ከማል አንድ ጨዋታ ሲቀጣ ቡድኑ አርባምንጭ ከተማ ደግሞ አምስት ተጫዋቾች የማስጠንቀቂያ ካርድ መመልከታቸውን ተከትሎ 5000 ብር እንዲቀጣ ተወስኖበታል።