የጣና ሞገዶቹ በዓይነቱ ለየት ያለ ስምምነት ፈጸሙ

የጣና ሞገዶቹ በዓይነቱ ለየት ያለ ስምምነት ፈጸሙ

ባህር ዳር ከተማ በዓይነቱ ለየት ያለውን የሚዲያ እና ኢቨንት አብሮ የመሥራት ስምምነት ተፈራርሟል።

ባህር ዳር ከተማ ስፓርት ክለብ በስፓርቱ ማርኬቲንግ በተለይም ወቅቱ የሚፈልገውን ዲጂታል ማርኬቲንግ ላይ የክለቡን ብራንድ መጠቀም የሚያስችለውን ስምምነት ከ “ዮቶጵያ” ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር ጋር ሲያከናውን ስምምነቱም እነዚህን ጉዳዮች እንደሚዳስስ ተመላክቷል።

1. የክለቡን አሰራር እና ዶክመንት አያያዝ ዲጂታላይዝ የማድረግ

በዚህ ስምምነት መሰረት ለባህር ዳር ከተማ በኢትዮጵያ እንደ ክለብ የመጀመሪያ የሚያደርገው ሶፍትዌር የተዘጋጀ ሲሆን ሶፍትዌሩ የክለቡ ደጋፊዎች ቀጥታ በኦንላይን ተመዝግበው የአባልነት ክፍያቸውን ፈፅመው መታወቂያቸውን ዲጂታሊ እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን የማልያ እና የመሳሰሉ የደጋፊዎች ቁሳቁሶችን ቀጥታ በኦንላይን ግዢ እንዲፈፅሙ የሚያስችል እንዲሁም የተጫዋቾችን የክለቡን መረጃ ዲጂታሊ ሰንዶ ለማስቀመጥ የሚረዳ ሆኖ የተዘጋጀ ነው።

ይህ ሶፍትዌር ከክለቡ በተጨማሪ ከተማዋን ለማስተዋወቅ ከፍተኛ ጥቅምን የሚሠጥ ሲሆን በተጨማሪም ደጋፊዎች አፕሊኬሽኑን በማውረድ ብቻ ሙሉ የክለባቸውን መረጃ ማለትም ውጤት ፣ ደረጃ ሰንጠረዥ እና የቀጣይ መርሐግብሮችን መረጃዎች ማግኘት ይችላሉ።

2. ወጥነቱ የተጠበቀ የማኅበራዊ ሚዲያ ማኔጅመንት ሥራ

ባህር ዳር ከተማ ስፓርት ክለብ እና የደጋፊዎች ማሕበር ወጥ እና አንድ የሆነ እንዲሁም ደረጃውን የጠበቀ የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እንዲኖራቸው የማድረግ ተግባር

3. ወርሐዊ ዲጂታል መፅሔት

በዚህ ስምምነት መሠረት ባህር ዳር ከተማ ከሰኔ ወር ጀምሮ ወርሐዊ የዲጂታል መፅሔት ይፋ የሚያደርግ ይሆናል።

መፅሔቱም የክለቡን ወርሐዊ መረጃወች እያቀረበ በየወሩ የሚቀጥል ይሆናል።

4. የኢቨንት ሥራ

ክለቡ እነዚህን ተግባራት በተሻለ መልኩ አፈፃፀም ይኖራቸው ዘንድ የሚያግዙ የኢቨንት ሥራወችን ከ “ዮቶጵያ” ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር ጋር የሚሰራ ይሆናል።

ስምምነቱ ግንቦት 20 የባህር ዳር ከተማ ስፓርት ክለቡ ከፍተኛ አመራሮች ሙሉ የቦርድ አባላት እንዲሁም የዮቶጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር ኃላፊዎች በተገኙበት ባህር ዳር ላይ ተፈፅሟል ።