በሦስት ዓመት ውስጥ ሁለቴ የሊጉ ኮከብ ግብጠባቂነትን ክብር ያገኘው የግብ ዘብ ለተጨማሪ ዓመታት ከቡድኑ ጋር ለመቆየት መስማማቱን ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች።
በአሰልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ የሚመሩት ኢትዮጵያ መድኖች ከፊታቸው ላለባቸው የአፍሪካ ቻምፕዮንስ ሊግ የቅድመ ማጣርያ ጨዋታ እና ለሀገር ውስጥ ውድድር በቂ የመዘጋጃ ጊዜ ለማግኘት ከትናንት በስትያ በአዳማ ከተማ ዝግጅታቸውን መጀመራቸው ይታወቃል። የቡድኑ አብዛኛው ቁልፍ ተጫዋቾችን ውላቸው የተጠናቀቀ መሆኑን ተከትሎ እነርሱን ለማቆየት በስራ ተደምጦ ያለው ቡድኑ የወሳኙን ግብጠባቂ ውል ለማራዘም መስማማታቸውን ሰምተናል።
ግብጠባቂው አቡበከር ኑራ በ2017 የውድድር ዘመን በብቸኝነት አንድም ደቂቃ ሳያልፍ በ33 ጨዋታዎች 3060 ዲቃዎችን በሜደ ላይ በማሳለፍ ከ34ቱ ጨዋታዎች በ21 ጨዋታዎች ምንም ጎል ሳይቆጠርበት የወጣ እና 15 ጎሎችን ብቻም በማስተናገድ ድንቅ ጊዜን ለቻምፒዮኖቹ አሳልፏል። አቡበከር ለሁለት ተጨማሪ ዓመት ከቡድኑ ጋር ለመቆየት የተስማማ ሲሆን ከዚህ ቀደም ለወሎ ኮምቦልቻ፣ ለጅማ ከተማ ፣ ለባህር ዳር ከተማ በመጫወት ሲያሳልፍ አቡበከር በሦስት ዓመት ውስጥ ሁለት ጊዜ የሊጉ ኮከብ ግብጠባቂ ክብርን በማሳካት ማሳለፉ ይታወቃል።