አሠልጣኝ ግርማ ወደ ሌላኛው የሊጉ ክለብ ለማምራት ከጫፍ ደርሰዋል

አሠልጣኝ ግርማ ወደ ሌላኛው የሊጉ ክለብ ለማምራት ከጫፍ ደርሰዋል

አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ ወደ ቢጫዎች ለማምራት ከጫፍ ደርሰዋል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከበርካታ ዓመታት በኋላ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ተመልሰው በ19 ነጥቦች በሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ሆነው ዓመቱን ብያጠናቅቁም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ሰኔ 28 በወሰነው ውሳኔ መሰረት በ2018 የውድድር ዓመት በሊጉ መሳተፋቸውን ያረጋገጡት ወልዋሎዎች ላለፉት ሳምንታት ዋና አሰልጣኝ ለመቅጠር ስያደርጉት የነበረው ሂደት ባለፉት ዓመታት ሀድያ ሆሳዕናን ያሰለጠኑት አሰልጣኝ ግርማ ታደሰን በመሾም ሊጠናቀቅ ከጫፍ ደርሷል።

ሶከር ኢትዮጵያ ከታማኝ ምንጮቿ ባገኘችው መረጃ መሰረት አሰልጣኙ ከክለቡ የበላይ አመራሮች ጋር ስያደርጉት የነበረው ድርድር በስምምነት ሊጠናቀቅ ከጫፍ የደረሰ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ሂደቱ ይገባደዳል ተብሎ ይጠበቃል።

ባለፉት ሦስት ዓመታት በዋና እንዲሁም በምክትል አሰልጣኝነት በሀድያ ሆሳዕና ቆይታ የነበራቸው አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ 2007 እንዲሁም 2011 ሀድያ ሆሳዕናን በ2010 ደግሞ ደቡብ ፖሊስን ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪምየር ሊግ ያሳደጉ ሲሆን በስልጤ ወራቤና ሀምበሪቾ ዱራሜም ቆይታ ማድረጋቸው ይታወቃል።