የጦና ንቦቹ የሦስት ተጫዋቾችን ውል አድሰዋል

የጦና ንቦቹ የሦስት ተጫዋቾችን ውል አድሰዋል

አዲስ አሰልጣኝ ወደ ቡድናቸው ለማምጣት በሂደት ላይ የሚገኙት ወላይታ ድቻዎች የሦስት ተጫዋቾቻቸውን ውል አድሰዋል።

ኢትዮጵያን ወክለው በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሚሳተፉት ወላይታ ድቻዎች ከፊታቸው ለሚጠብቃቸው አህጉራዊ እና ለቀጣዩ ዓመት የውድድር ዘመን ራሳቸውን ለማጠናከር የአሰልጣኝ ቅጥርን ከመፈፀማቸው በፊት በቡድኑ ውስጥ ውላቸው የተጠናቀቁ ወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን ውል ማራዘምን ቅድሚያ በመስጠት የሦስት ተጫዋቾቻቸውን ውል በማደስ የዝውውር ስራቸውን “ሀ” ብለው ጀምረዋል።

ከክለቡ ታዳጊ ቡድን የተገኙት የቀኝ መስመር ተከላካዩ ኬኔዲ ከበደ እና በአጥቂነት እና በመስመር አጥቂነት ቡድኑን ሲያገለግል የነበረው ዮናታን ኤልያስ እንዲሁም ደግሞ በሰንዳፋ በኬ ፣ ቡታጂራ ከተማ ፣ ገላን ከተማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከተጫወተ በኋላ ላለፈው አንድ ዓመት በጦና ንቦቹ ቤት ያሳለፈው አጥቂው መሳይ ሠለሞን ውላቸውን ያራዘሙ ተጫዋቾች ሆነዋል።