ወልዋሎ በይፋ አሰልጣኝ ቀጥሯል

ወልዋሎ በይፋ አሰልጣኝ ቀጥሯል

አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ የወልዋሎ አዲሱ አሰልጣኝ በመሆን ተሹመዋል።

በትናንትናው ዕለት የቀድሞ የሀድያ ሆሳዕና አሰልጣኝ የሆኑት አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ ወልዋሎን ለመረከብ ከጫፍ መድረሳቸው መግለፃችን ይታወሳል። አሁን ደግሞ ክለቡ በይፋ አሰልጣኙን መቅረጠሩን ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል።

ከክለቡ የበላይ አመራሮች ጋር ቀናትን የፈጀ ድርድር በማድረግ ላይ የቆዩት አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ ባለፉት ሦስት ዓመታት በዋና እንዲሁም በምክትል አሰልጣኝነት በሀድያ ሆሳዕና ቆይታ የነበራቸው ሲሆን በ2007 እና 2011 ሀድያ ሆሳዕናን እንዲሁም በ2010 ደግሞ ደቡብ ፖሊስን ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪምየር ሊግ ማሳደግ ችለዋል። አሁን ደግሞ ከስልጤ ወራቤ፣ ሀምበርቾ ፣ ደቡብ ፖሊስ እና ሀድያ ሆሳዕና በኋላ ቢጫዎቹን ለማሰልጠን ቡድኑን ተረክበዋል።