ረመዳን የሱፍ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ይቀጥላል

ረመዳን የሱፍ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ይቀጥላል

ሁለገቡ ተጫዋች ከቻምፕዮኖቹ ጋር ያለውን ውል ለማራዘም ከስምምነት ደርሷል።


ሁለት የሊግ ዋንጫዎች ካነሳበት ውጤታማው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቆይታ በኋላ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ኢትዮጵያ መድንን ተቀላቅሎ ሦስተኛ የሊግ ዋንጫውን ማሳካት የቻለው ረመዳን የሱፍ ከቻምፕዮኖቹ ጋር ያለውን ውል ለማራዘም ከስምምነት ደርሷል። በ2017 የውድድር ዓመት በግራ መስመር ተከላካይነት እንዲሁም በመስመር አጥቂነት በ 25 ጨዋታዎች ተሰልፎ ሰባት ግቦች ከመረብ ማዋሀድ የቻለው ሁለገቡ ተጫዋች ባለፉት ቀናት ከኢትዮጵያ መድን ጋር ያለውን ውል ለማራዘም ስያደርገው የነበረውን ድርድር በስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ በክለቡ ለመቆየት የተስማማ ሰባተኛ ተጫዋች ሆኗል።


በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተስፋ ቡድን እንዲሁም በብሄራዊ ሊጉ ንስር ቆይታ አድርጎ ከ2011 አጋማሽ ጀምሮ ደግሞ በተለያዩ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች መጫወት የቻለው ረመዳን ከዚ ቀደም በስሑል ሽረ፣ ወልቂጤ ከተማ፣ ሁለት የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ያነሳበት ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን መጫወት ችሏል።