ሸገር ከተማ የተከላካይ አማካይ አስፈረመ

ሸገር ከተማ የተከላካይ አማካይ አስፈረመ

ሸገር ከተማዎች በዝውውሩ ንቁ ተሳትፎ ማድረጋቸውን ቀጥለው የተከላካይ አማካይ የስብስባቸው አካል ማድረግ ችለዋል።

አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን በዋና አሰልጣኝነት በመቅጠር በዝውውሩ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የሚገኙት አዲስ አዳጊዎቹ ሸገር ከተማዎች አሁን ደግሞ ባለፉት አራት ዓመታት በሀዋሳ ከተማ ቆይታ የነበረው ዓብዱልበሲጥ ከማልን አስፈርመዋል።

ከኢትዮጵያ ቡና ታዳጊ ቡድን ከተገኘ በኋላ በአሳዳጊ ክለቡ ዋናው ቡድን፣ ደደቢት፣ ሰበታ ከተማ እንዲሁም በሀዋሳ ከተማ ቆይታ የነበረው ይህ ተጫዋች በቀጣይ ዓመት ደግሞ በአዲስ አዳጊዎቹ ቤት ለመጫወት ከስምምነት ደርሷል።