ሸገር ከተማዎች የሁለት ተጫዋቾች ፊርማ አግኝተዋል

ሸገር ከተማዎች የሁለት ተጫዋቾች ፊርማ አግኝተዋል

ሸገር ከተማዎች ሁለት የፊት መስመር ተጫዋቾች ከታችኞቹ ሊጎች አስፈርመዋል።

ሸገር ከተማ በዝውውሩ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ቀደም ብለው ካሌብ በየነ፣ ዓብዱልበሲጥ ከማል እና ቡልቻ ሹራን በማስፈረም በርከት ያሉ ነባር ተጫዋቾች ውል ያራዘሙ ሲሆን አሁን ደግሞ ሁለት የፊት መስመር ተጫዋቾች ወደ ቡድናቸው ቀላቅለዋል።

የመጀመርያው ፈራሚ ገመዳ ማሞ ነው። ከጉጂ ዞን የተገኘው እና በቅርቡ በተጠናቀቀው የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና በደምቢ ዶሎ መለያ አራት ግቦችን በማስቆጠር ክለቡ ወደ 2018 የኢትዮጵያ ሊግ አንድ እንዲያድግ አስተዋጾ ያደረገና የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ የተሸለመው ተጫዋቹ አሁን ደግሞ በፕሪምየር ሊጉ ተሳታፊ ለሆነው ሸገር ከተማ ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል።

ሁለተኛው ቡድኑን የተቀላቀለው ተጫዋች ደግሞ ከቤ ብዙነህ ነው። በመስመር አጥቂነት የሚሰለፈው ወጣቱ ተጫዋች ከአምቦ ጎል ፕሮጀክት ከወጣ በኋላ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሱሉልታ ክ/ከተማ ስኬታማ ጊዜ ያሳለፈ ሲሆን አሁን ደግሞ በአሰልጣኝ
አሸናፊ በቀለ ለሚሰለጥነው ሸገር ከተማ ፊርማውን አኑሯል።