ድሬዳዋ ከተማዎች ሦስተኛ ፈራሚያቸውን አግኝተዋል።
በአሰልጣኝ ይታገሱ የሚመሩት ድሬደዋ ከተማዎች ቀደም ብለው ሬድዋን ሸሪፍ እና ጃዕፈር ሙደሲርን በማስፈረም የአቤል አሰበን ውል ያራዘሙ ሲሆን አሁን ደግሞ ያብስራ ሙልጌታን የዝውውር መስኮቱ ሦስተኛ ፈራሚያቸውን አድርገዋል።
ባለፈው ውድድር ዓመት በወልዋሎ ቆይታ የነበረው እና በውድድር ዓመቱ በ26 ጨዋታዎች ተሳትፎ 2269′ ደቂቃዎችን ቢጫዎቹን በጥሩ ሁኔታ ያገለገለው ይህ ተጫዋች ከዚህ ቀደም በቅዱስ ቅዮርጊስ ታዳጊና ዋና ቡድን፤ በ2013 ደግሞ አሳዳጊ ክለቡን ለቆ ለጅማ አባጅፋር፣ መቻል፣ ሻሸመኔ እንዲሁም በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በወልዋሎ መጫወቱ ሲታወስ ለቡርትካናማዎቹ ለሁለት አመት ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል።