አቤሴሎም ዘመንፈስ ተሸለመ

አቤሴሎም ዘመንፈስ ተሸለመ

በአሜሪካው ክለብ የሚጫወተው ኢትዮጵያዊ የምዕራብ ኮንፈረንስ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች የሚል ሽልማት ተጎናፀፈ።

በውድድር ዓመቱ መጀመርያ ለአሜሪካው ክለብ ባላርድ ፌርማውን ያኖረው ኢትዮጵያዊው አቤሴሎም ዘመንፈስ የምዕራብ ኮንፈረንስ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች በሚል ተሸልሟል።

በመቐለ ከተማ የተወለደው እና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ቡድን ማገልገል የቻለው ይህ ተስፈኛ አማካይ ባለፈው ዓመት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ካደረጉት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ በኋላ ከቡድኑ ተለይቶ ተቀማጭነቱ ሲያትል ከተማ ላደረገው ባላርድ ፌርማውን ማኖሩ ሲታውስ በሀገሪቱ የመጀመርያ ዓመት ቆይታውም በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አግኝቷል።

በውድድር ዓመቱ በአማካይነት እንዲሁም በተከላካይነት በሁሉም ጨዋታዎች በቋሚነት የጀመረው ተጫዋቹ ቡድኑ እስከ ‘Usl league two’ ፍፃሜ ድረስ ባደረገው ጉዞ የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋች በመሆን በሊጉ ምርጥ ቡድን ከመካተት አልፎ የሊጉ ምርጥ ተጫዋች የሚል ሽልማትም ተጎናፅፏል።