ሸገር ከተማዎች አማካይ አስፈርመዋል

ሸገር ከተማዎች አማካይ አስፈርመዋል

ባለፉት አራት ዓመታት በፈረሰኞቹ ቤት ቆይታ የነበረው አማካይ አዲስ አዳጊውን ክለብ ተቀላቀለ።

በዛሬው ቀን በርከት ያሉ ዝውውሮች ያገባደዱት አዲስ አዳጊዎቹ ሸገር ከተማዎች አሁን ደግሞ ባለፉት ዓመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ቆይታ የነበረው አማካዩ በረከት ወልዴን አስፈርመዋል።

ከወላይታ ድቻ ታዳጊ ቡድን ካደገ በኋላ እናት ቡድኑን አራት ዓመት ባለፉት አራት ዓመታት ደግሞ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቆይታ የነበረው ይህ ተጫዋች ከክለብ እግር ኳስ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ማገልገሉ ሲታወስ አሁን ደግሞ አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማን ለመቀላቀል ፊርማውን አኑሯል።