ሸገር ከተማ ግብ ጠባቂ አስፈረመ

ሸገር ከተማ ግብ ጠባቂ አስፈረመ

ከታዳጊ እስከ ዋናው ቡድን ቅዱስ ጊዮርጊስን ያገለገለው ግብ ጠባቂው ወደ ሸገር ከተማ አምርቷል።

ከዚህ ቀደም ካሌብ በየነ፣ ቡልቻ ሹራ፣ ዓብዱልበሲጥ ከማል፣ ገመደ ማሞ፣ ከቤ ብዙነህ እና በረከት ወልዴን በማስፈረም በርከት ያሉ ነባር ተጫዋቾች ውል ያራዘሙት ሸገር ከተማዎች አሁን ደግሞ ግብ ጠባቂውን ባህሩ ነጋሽ አስፈርመዋል።

ከተስፋ ቡድን ካደገ በኋላ ባለፉት ስምንት ዓመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ዋናው ቡድን ማገልገል የቻለው ግብ ጠባቂው ባለፈው የውድድር ዓመት በ24 ጨዋታዎች ተሰልፎ 2056 ደቂቃዎች ፈረሰኞቹን ያገለገለ ሲሆን ለሸገር ከተማ መፈረሙን ተከትሎም በክለብ እግር ኳስ ሂወቱ ለመጀመርያ ጊዜ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ማልያ ውጭ የሚለብስ ይሆናል።