ብርቱካናማዎቹ አጥቂ አስፈርመዋል

ብርቱካናማዎቹ አጥቂ አስፈርመዋል

በአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ የሚመሩት ድሬደዋ ከተማዎች አራተኛ ፈራሚያቸውን አግኝተዋል።

ድሬደዋ ከተማዎች አስቀድመው ወደ ዝውውሩ በመግባት ሬድዋን ሸሪፍ፣ ጃዕፋር ሙደሲር እና ያብስራ ሙሉጌታን ሲያስፈርሙ የአቤል አሰበን ውል ማራዘማቸው ይታወቃል። ቡድናቸውን ለማጠናከር በመቀጠል የመስመር አጥቂውን አቤል ነጋሽን ለማስፈረም መስማማታቸውን አውቀናል።

የእግርኳስ ህይወቱን በመቻል ታዳጊ ቡድን አስከ ዋናው ቡድን ከዘለቀ በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ እንዲሁም ወልቂጤ ከተማ ያሳለፈው የመስመር አጥቂው በድጋሚ ከሁለት ዓመት በፊት ወደ አሳዳጊው መቻል በመመለስ ሲጫወት ቆይቶ አሁን የብርቱካናማዎቹን መለያ የሚለብስበትን የሁለት ዓመት ውል ፈርሟል።