የከፍተኛ ሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ቢጫዎቹን ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል።
አሰልጣኝ ግርማ ታደሰን በዋና አሰልጣኝነት ቀጥረው ፍሬው ሰለሞን፣ በየነ ባንጃው፣ ኢብራሂም መሐመድ እና ፍሬዘር ካሳን ለማስፈረም የተስማሙት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ ከአዲሱ አቱላ ጋር በጣምራ የከፍተኛ ሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ
ያጠናቀቀውን ጌትነት ተስፋዬን ለማስፈረም ተስማምተዋል።
በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በወልቂጤ ከተማ መለያ 13 ግቦችን ከመረብ ጋር ያዋሀደው አማካዩ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ መድን፣ ሻሸመኔ ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ መጫወት የቻለ ሲሆን በተለይም በሰራተኞቹ ቤት ቆይታው በግሉ ድንቅ የውድድር ዓመት አሳልፏል። አሁን ደግሞ በቀጣይ የውድድር ዓመት በቢጫው መለያ ለመጫወት የክለቡ አምስተኛ ፈራሚ ለመሆን ከስምምነት ደርሷል።