ሽመክት ጉግሳ ወደ ሽረ ምድረ ገነት አመራ

ሽመክት ጉግሳ ወደ ሽረ ምድረ ገነት አመራ

ሽረ ምድረ ገነት ሁለገብ ተጫዋቹን የግሉ አድርጓል።

ቀደም ብሎ በዝውውሩ መስኮቱ መክብብ ደገፉ፣ ተካልኝ ደጀኔ፣ በኃይሉ ግርማ፣ ቢኒያም ላንቃሞ፣ ፀጋአብ ዮሐንስ፣ አቤል ማሙሽ፣ አዲስ ተስፋዬ እና ስንታየሁ ዋለጬን ያስፈረመው ሽረ ምድረ ገነት አሁን ደግሞ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በኢትዮ ኤሌክትሪክ ቆይታ የነበረው ሁለገቡ ሽመክት ጉግሳን አስፈርሟል። በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከስድስት ዓመታት የፋሲል ከነማ ቆይታ በኋላ ወደ ኤሌክትሪክ አምርቶ በዓመቱ በ30 ጨዋታዎች ተሳትፎ 2323′ ደቂቃዎች ያገለገለው ተጫዋቹ ከአንድ ዓመት የቡድኑ ቆይታ በኋላ ወደ ሽረ ምድረ ገነት ለማምራት ፊርማውን አኑሯል።

በ2011 ደደቢትን ለቆ ወደ ዐፄዎቹ ቤት በማምራት ለስድስት ዓመታት ፋሲል ከነማን በማገልገል ወደ ኤሌክትሪክ አምርቶ አንድ የውድድር ዓመት ከቡድኑ ጋር የቆየው ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨምሮ ወላይታ ድቻ፣ አየር ኃይል፣ ሀዋሳ ከተማ እና ደደቢት መጫወቱ ይታወሳል።