የኢትዮጵያ ቡና እና የዋልያዎቹ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ቶክ ጀምስ ከክለቡ ኢትዮጵያ ቡና ጋር የተፈጠረው አለመግባባት አሁንም ቀጥሏል፡፡ ቶክ ከቡና የወጣት ቡድን በ2004 ዋናውን ቡድን የተቀላቀለ ሲሆን፡፡ በአዲሱ ህግ መሰረት ለአንድ ተጨማሪ አመት ቡናን ማገልገል እንዳለበት በመግለፅ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን ቶክ ለቡና እንዲጫወት የወሰነ ቢሆንም ተጫዋቹ ግን የቆይታ ውሌን ስለጨረስኩ ከክለቡ ጋር መለያየት አለብኝ በሚለው አቋሙ ፀንቷል፡፡
አዲሱ የውድድር ዘመን ከተጀመረ ጀምሮ አንድም ጨዋታ ላይ ለኢትዮጵያ ቡና ያልተጫወተው ቶክ ጄምስ ጉዳዩ በቅርብ ጊዜ ውስጥ የማይፈታ ከሆነ ወደ ቤተሰቦቹ ለመሄድ መወሰኑንና ትምህርቱም ላይ ትኩረት እንደሚደርግ ተናግሯል፡፡
ቶክ ለመጨረሻ ጊዜ ጨዋታ ያደረገው ዋሊያዎቹ የመጀመሪያውን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከአልጄርያ ጋር ሲጫወቱ ሰሆን ኢትዮጵያ ቡና የተከላካዩን አለመኖር አስመልክቶ ለሚፈጠረው ቀዳዳ በማሰብ ኤፍሬም ወንድወሰንን ከዳሽን ቢራ እና ካሜሮናዊውን ኦሊቨር ዋረንን በክረምቱ የዝውውር መኮስት ማስፈረሙ የሚታወስ ነው፡፡
ምንጭ – ፕላኔት ስፖርት