መቐለ 70 እንደርታ የመስመር አጥቂውን ለማስፈረም ተስማምቷል

መቐለ 70 እንደርታ የመስመር አጥቂውን ለማስፈረም ተስማምቷል

ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቆይታ የነበረው ተጫዋች ወደ ምዓም አናብስት ለማምራት ተስማምቷል።


አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊትን በዋና አሰልጣኝነት ቀጥረው ሱሌይማን ሐሚድ፣ መሐሪ አመሀ፣ አብዲ ዋበላ፣ አሰጋኸኝ ጴጥሮስ፣ ብርሀኑ አዳሙ፣ ጊትጋት ኩት፣ ፍፁም ዓለሙ እና ፍሬዘር ካሳን ለማስፈረም ተስማምተው የኬኔዲ ገብረፃዲቕ፣ ዘረሰናይ ብርሀነ እና የአሸናፊ ሀፍቱን ውል ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለማራዘም የተስማሙት መቐለ 70 እንደርታዎች አሁን ደግሞ ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቆይታ የነበረው የመስመር ተጫዋቹ ኪታካ ጅማን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።


በ2016 የሀምራዊ ለባሾቹ የመጀመርያ ዓመት ቆይታው ላይ የሊጉን ዋንጫ ያሳካው እና በተጠናቀቀው ዓመት በ34 ጨዋታዎች ተሳትፎ 2811′ ደቂቃዎች ቡድኑን በማገልገል 9 ግቦች ያስቆጠረው ተጫዋቹ ከኢትዮጵያ ቡና ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ በገላን ከተማ በኢትዮጵያ መድን እንዲሁም ያለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቆይታ ማድረጉ ይታወቃል። አሁን ደግሞ ከሀምራዊ ለባሾቹ ጋር ያለውን ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ምዓም አናብስቱ ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል።