ሶፎንያስ ሰይፈ ከምዓም አናብስት ጋር ለመቀጠል ከስምምነት ደርሷል።
ቀደም ብለው ኪቲካ ጅማን ለማስፈረም የተስማሙት እና በዝውውር መስኮቱ አስር አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው ቀላቅለው የኬኔዲ ገብረፃድቕ፣ አሸናፊ ሀፍቱ እና ዘርኸሰናይ ብርሃነን ውል ለማራዘም የተስማሙት ምዓም አናብስት አሁን ደግሞ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ጥሩ ጊዜ ያሳለፈውን ግብ ጠባቂያቸው ሶፎንያስ ሰይፈን ውል ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለማራዘም ከስምምነት ደርሰዋል።
በ2016 በከፍተኛ ሊጉ ንብ ቆይታ ካደረገ በኋላ በ2018 ወደ ቡድኑ ዳግም የተመለሰው ተጫዋቹ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በ34 ጨዋታዎች ተሳትፎ 3058′ ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለ ሲሆን ከዚህ ቀደም በደደቢት ወጣትና ዋናው ቡድን፣ ገላን ከተማ እንዲሁም ንብ መጫወቱ የሚታወቅ ሲሆን በ2009 አጋማሽ መቐለ 70 እንደርታን ከተቀላቀለ ወዲህ ቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊግ ሲገባ እንዲሁም የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ስያሳካ የስብስቡ አካል መኖሩ ይታወሳል።