በአሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ የሚመራው ሽረ ምድረ ገነት የመሃል ተከላካዩን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል።
በዝውውር መስኮቱ መክብብ ደገፉ፣ ተካልኝ ደጀኔ፣ በኃይሉ ግርማ፣ ፀጋአብ ዮሐንስ፣ ቢንያም ላንቃሞ፣ አዲስ ተስፋዬ፣ ስንታየሁ ዋለጬ፣ አቤል ማሙሽ፣ ሽመክት ጉግሳ እና ዳንኤል ዳርጌን በማስፈረም በመቀመጫ ከተማቸው ሽረ እንዳሥላሴ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን የጀመሩት ሽረ ምድረ ገነቶች አሁን ደግሞ የመሃል ተከላካዩ አንተነህ ተስፋዬን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።
በአርባምንጭ ከተማ እግር ኳስን ጀምሮ በክለቡ የአራት ዓመታት ቆይታ ካደረገ በኋላ በሲዳማ ቡና፣ ድሬዳዋ ከተማ፤ ሰበታ ከተማ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንዲሁም እስከ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ዳግም ወደ ሲዳማ ቡና ተመልሶ በመጫወት ላይ የቆየው የመሀል ተከላካዩ አሁን ደግሞ ከአራት ዓመታት የሲዳማ ቡና ቆይታ በኋላ በአሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ ወደ ሚሰለጥነው ሽረ ምድረ ገነት ለመቀላቀል ተስማምቶ ዛሬ ማምሻውን ወደ ሽረ እንዳሥላሴ ተጉዞ ስብስቡን ይቀላቀላል።