ወልዋሎዎች የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቀቁ

ወልዋሎዎች የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቀቁ

በአዳማ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በማከናወን ላይ የሚገኙት ቢጫዎቹ ሁለት ተጫዋቾች አስፈርመዋል።

በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ፍሬው ሰለሞን፣ በየነ ባንጃው፣ ኢብራሂም መሐመድ፣ ሰመረ ሀፍታይ፣ ጌትነት ተስፋዬ፣ ፍቃዱ መኮንን፣ ነፃነት ገብረመድኅን ፣ ሙሉዓለም መስፍን፣ ኮንኮኒ ሀፊዝን እና ወጋየሁ ቡርቃን ለማስፈረም ተስማምተው  የኪሩቤል ወንድሙ፣ ናሆም ኃይለማርያም፣ ሱልጣን በርኸ፣ ስምዖን ማሩ፣ ሚክኤለ ኪዳኑ፣ ናትናኤል ኪዳነ እና የዳዊት ገብሩን ውል ለማራዘም የተስማሙት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ ሁለት ተጫዋቾች አስፈርመዋል።

ቀዳሚው ወደ ቢጫዎቹን ያመራው ግብ ጠባቂው ስንታየሁ ታምራት ነው፤ ከዚህ ቀደም በደደቢት፣ ሀላባ ከተማ፣ ወልድያ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕና መጫወት የቻለው ግብ ጠባቂው ከነብሮቹ ጋር ያለውን ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ወልዋሎ
አምርቶ በቅድመ ውድድር ዝግጅት ከቡድኑ ጋር በዝግጅት ይገኛል። ሁለተኛው ወደ ቡድኑ ያመራውና በቅድመ ውድድር ዝግጅት ስብስቡን የተቀላቀለው ተጫዋች ደግሞ ባለፉት ዓመታት በከፍተኛ ሊጉ ኦሜድላ ቆይታ የነበረውና በ2017 ውድድር ዓመት ጥሩ እንቅስቃሴ ያደረገው የመስመር ተጫዋቹ እንዳልካቸው ጥበቡ ነው።