ያለፉትን ዓመታት በባህር ዳር ከተማ ቆይታ ያደረገው ሁለገቡ ተጫዋች የቀድሞ ክለቡን ለመቀላቀል ተስማምቷል።
የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ከጀመሩ ቀናቶች ያስቆጠሩት እና ወደ መጨረሻዎቹ አካባቢ በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ዝውውሩ በመግባት ባልተጠበቀ ሁኔታ ጠንካራ ያሉ ዝውውሮችን የፈፀሙት አዳማ ከተማዎች አሁን ደግሞ ግዙፉን ሁለገብ ተጫዋች ሙጂብ ቃሲምን የግሉ ለማድረግ ተቃርቧል።
በሲዳማ ቡና የአማካይ ስፍራ ተጫዋች በመሆን የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው ሙጂብ ቃሲም በማስከተል ሀዋሳ ከተማ፣ በአዳማ ከተማ በኋላ ጥሩ ቆይታን ካደረገበት ፋሲል ከነማ ጋር የሊጉን ዋንጫ ያነሳው ሙጂብ ወደ አልጄሪያ ሊግ በማቅናት የወራት ቆይታን ካደረገ በኋ የቀድሞ ክለቡ ሀይቆቹን በድጋሚ በመቀላቀል መጫወቱ ይታወሳል። በማስከተል በባህር ዳር ከተማ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ቆይታ የነበረው ሁለገቡ ተጫዋች ባሳለፍነው የውድድር ዘመን ተከላካይም አጥቂም ሆኖ በ25 ጨዋታዎች ተሳትፎ 2002 ደቂቃዎች ቡደኑን በማገልገል ስድስት ጎሎችን አስቆጥሯል።
ተጫዋቹ ግብ ጠባቂ፣ ተከላካይ እና አጥቂ ሆኖ ወደ ተጫወተበት አዳማ ከተማ ለማምራት ተስማምቷል። ትናት ጠዋት በጂም ከሰዓት በሜዳ ላይ ከቡድኑ ጋር ልምምድ መስራቱንም ሰምተናል።