ያለፉትን ስድስት ወራት ከፋሲል ከነማ ጋር ቆይታ የነበረው ግብ ጠባቂ በስምምነት መለያየቱ ተሰምቷል።
በ2017 የውድድር ዘመን ሽረ ምድረ ገነት ቤት አምረቶ ለስድስት ወር በዘጠኝ ጨዋታዎች ግልጋሎት የሰጠው ግብ ጠባቂው ፋሲል ገብረሚካኤል በውድድሩ አጋማማሽ ከቡድኑ ጋር በስምምነት ከተለያየ በኋላ ለአንድ ዓመት ቆይታ ዐፄዎቹን ተቀላቅሎ ነበር።
ሆኖም ከፋሲል ከነማ በስድስት ወር ቆይታ በ13 ጨዋታዎች ላይ ተሳትፎ ካደረገ በኋላ አሁን በስምምነት መለያየቱ ታውቋል። ፋሲል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በተለያዮ ዕድሜ እርከኖች መጫወቱ ሲታወቅ በዳሽን ቢራ ፣ በሰበታ ከተማ፣ በባህር ዳር ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ፣ በሽረ ምድረ ገነት እንዲሁም በፋሲል ከነማ ክለቦች ተጫውቶ አሳልፏል።